Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

500 ሰዎች ብቻ የሚኖሩባት የዓለማችን እጅግ ቀዝቃዛዋ መንደር – ኦይሚያኮን

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሩሲያ ግዛት በሳይቤሪያ አካባቢ የምትገኘዋን 500 ሰዎች ብቻ የሚኖሩባትን የዓለማችንን እጅግ ቀዝቃዛዋን መንደር እናስተዋውቃችሁ፡፡

አነስተኛዋና ቀዝቃዛዋ መንደር ኦይሚያኮን ትባላለች፡፡

የኦይሚያኮን መንደር ዓመታዊ አማካኝ የቅዝቃዜ መጠን ከዜሮ በታች 16 ዲግሪ ሴሊሺየስ ነው፡፡

ትንሿ መንደር በፈረንጆቹ 1933 ላይ ከዜሮ በታች 68 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሆነ እጅግ ዝቅተኛውን የቅዝቃዜ መጠን አስመዝግባለች፡፡

መንደሯ ከመቀዝቀዟ የተነሳ በሥፍራው ቧንቧ ቢዘረጋም ውሃው ስለማይወርድ ነዋሪዎቹ የሽንት ቤት እና የሻወር አገልግሎት ለማግኘት የውሃ ማጠራቀሚያ መስቀል ግድ ብሏቸዋል፡፡

በሥፍራው ምንም ዓይነት አዝዕርት ስለማይበቅል ፣ የሰውነታቸውንም ሙቀት ለመጠበቅ ግድ ስለሚላቸው የአካባቢው ሰዎች ሁልጊዜም ስትሮጋኒያ የተሰኘ የቀዘቀዘ ጥሬ ዓሳ እና የሚያረቧቸውን እንስሳት ሥጋ ይመገባሉ፡፡

የመንደሯ ነዋሪዎች በአስቸጋሪው የክረምት ወራት በቀን ካለው 24 ሠአታት ውስጥ 21ዱን ሠዓት በጨለማ ውስጥ እንደሚያሳልፉ ታይምስ ትራቭል እና ብሩት ኔቸር ጽፈዋል፡፡

የፈረንጆቹ ጥር ወር መንደሯ ከዜሮ በታች 47 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሚደርሰውን እጅግ ቀዝቃዛ የዓየር ንብረት የምታስመዘግብበት እና ነዋሪዎቿ እስከ መደንዘዝ የሚደርሱበት ወቅት እንደሆነም ይነገራል፡፡

የመንደሯ ነዋሪዎች አንድ ጊዜ የመኪናዎቻቸውን ሞተር ካጠፉ ድጋሚ ለማስነሳት ስለሚያስቸግራቸው ሁልጌዜም የመኪናዎቻቸውን ሞተር ሳያጠፋ ይተውታል፡፡

ወይም ደግሞ መኪናዎቻቸውን ጋራጆቻቸው ውስጥ አቁመው ሙቀት እንዲያገኝ እሳት ያቀጣጥላሉ ተብሏል፡፡መንደሯ ምድራችን ላይ የሰው ልጅ የሚኖርባት እጅግ ቀዝቃዛዋ ስትሆን አመዳይ (ውርጭ) ደግሞ መለያዋ ነው።

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version