Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት ስምንት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት ሥምንት ወራት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው የግብር ትምህርት እና ኮሙኒኬሽን የሥራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ አግማስ ጫኔ እንዳሉት÷ ለመሰብሰብ የታቀደው ገቢ የክልሉን የበጀት ፍላጎት በ45 በመቶ ይሸፍናል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ከ340 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ያሉ ሲሆን ÷ከዚህም ውስጥ ከ18 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ውስጥም 7 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደ ሲሆን÷ እስካሁን 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወይም 60 በመቶ ያህሉ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

አቶ አግማስ የኑሮ ውድነትን፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄንና የሥራ አጥነት ጥያቄን ለመመለስ ግብር ከፋዩ ግብር መክፈል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ዘመናዊነትን የተከተለ የግብር አከፋፈል ሥርዓት ለመዘርጋት እና የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልስ ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችል አሠራር ለመጀመር እቅድ ተይዞ እየሰራ እንደሆነም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version