አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታ አካላት የደንብ ልብስን በሀገር ውስጥ በማምረት 60 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የጸጥታ ተቋማት የአልባሳት አቅርቦት አፈጻጸም ላይ ከፌዴራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ከውጪ ይገቡ የነበሩ ያለቀላቸው ምርቶችን ጥራታቸውን በጠበቁ የሀገር ውስጥ ምርቶች በመተካት የእሴት ጭማሬውን 62 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
የጸጥታ ተቋማት የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ በመተካት ሂደት ላይ እስካሁኑ ከ18ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል፡፡
በምርቱ ላይ 18 ፋብሪካዎች የተሳተፉ መሆናቸውን እና 60 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!