Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት በሳይበር ደኅንነት ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አቶ ሰለሞን የኢትዮጵያ መንግስት ከሩሲያ መንግስት ጋር በተለያዩ የልማት ዘርፎች እያከናወናቸው የሚገኘውን ጠንካራ የትብብር ስራዎች በሳይበር ደኅንነት ዘርፍ መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

 

አምባሳደር ኢቭጌኒ÷ አስተዳደሩ የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነት በማረጋገጥ የሀገሪቷን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ከመደገፍ አንፃር እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት በሌሎች የልማት ዘርፎች ያላቸውን ጠንካራ ትብብር በሳይበር ደኅንነት ዙሪያ በመድገም የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡

ለዚህም ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚያደርጉም አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version