የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከ5 ሺህ በላይ ታክሲዎች ለኩላሊት ህመምተኞች ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

By Tibebu Kebede

April 15, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህመምተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከ5 ሺህ በላይ ታክሲዎች ለህመምተኞቹ ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለፀ።

የነጻ የትራስፖርት አገልግሎቱን መስጠት የጀመሩትም ዘሉሲ ሜትር ታክሲና ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች ማህበር አባላት ናቸው።