Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በእህትማማች ከተሞች ግንኙነትና በባህል ልውውጥ ዙሪያ መምከራቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በከተማ ግብርና እና በሌሎች የተለያዩ ዘርፎች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ከእስራኤል ጋር ያለውን የረጅም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንሰራለንም ብለዋል ከንቲባ አዳነች፡፡

Exit mobile version