አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በዓለም ባንክ ድጋፍ በ”ዩ አይ አይ ዲፒ” ፕሮግራም እየተከናወነ በሚገኘው የዘመናዊ ቄራ አገልግሎት ዙሪያ መክረዋል።
አቶ ኦርዲን ÷ግንባታው የተጠናቀቀውን የዘመናዊ የቄራ አገልግሎት ወደ ስራ ለማስገባት በቅንጅትና መስራት እና ለስራው ስኬታማነትም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የቄራ ግንባታው አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶለት ስራ እንዲጀምር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክትትልና የድጋፍ ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ለስራው ስኬታማነት ከካሳ ክፍያ ፣ የህግ የበላይነት ከማረጋገጥና መሰል ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተገቢው መንገድ መቅረፍ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የዘመናዊ የቄራ አገልግሎትን ስራ ለማስጀመርና አገልግሎተን ተደራሽ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ሚኒስቴሩና ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን የድጋፍና የክትትል ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ያ መረጃ ያመላክታል፡፡