ስፓርት

ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን ረቱ

By ዮሐንስ ደርበው

April 02, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ 17ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ ግብሮች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨሲቲ ስታዲየም ተካሂደዋል፡፡

ዐፄዎቹ ከወላይታ ድቻ ጋር 9፡00 ላይ ባደረጉት ጨዋታ 2 ለ1 አሸንፈዋል፡፡

ፋሲል ከነማ ከመመራ ተነስቶ ነው ኦሴ ማውሊ በ68ኛው እና 82 ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች ማሸነፍ የቻለው፡፡

ቃልኪዳን ዘላለም በፍጹም ቅጣት ምት በ41ኛው ደቂቃ ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

እንዲሁም ምሽት 12፡00 ሰዓት ላይ በተካሄደ ሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ጎሎቹን እስማኤል ኦሮ አጎሮ እና ሀይደር ሸረፋ አስቆጥረዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!