Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከለውጡ በኋላ የተገኙ ድሎችና ስኬቶችን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
 
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
Exit mobile version