Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲንጋፖር በድጋሚ የቀጥታ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ሲንጋፖር ለሶስት ዓመት አቋርጦት የነበረውን የቀጥታ በረራ በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ።

በዓለም የንግድ ማዕከልነታቸው ከሚጠቀሱት መካከል አንዷ የሆነችው ሲንጋፖር ከተማ በረራ ያደረገው አውሮፕላን ቻንጊ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀበባል እንደተደረገለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

በረራው አየር መንገዱ በእስያ ያለውን ተደራሽነት እንዲሁም በአፍሪካ እና ሲንጋፖር መካከል ጉዞ ለሚያደርጉ ተጓዦች የአየር ትስስርን እንደሚያሰፋ ተገልጿል።

በአፍሪካ እና ሲንጋፖር መካከል በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማሳደግ ያለው ፋይዳ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

የበረራ አገልግሎቱን በሳምንት አራት ጊዜም እንደሚሰጥ የገለፀው አየር መንገዱ ከ130 በላይ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች እና የካርጎ መዳረሻዎች እንዳሉት አስታውቋል።

Exit mobile version