የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን ለአንባቢያን ተደራሽ የሚያደርግ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

March 31, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን ለአንባቢያን ተደራሽ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መርሐ-ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከመጽሐፍ የሚገኘው ገቢ ደረጃውን ለጠበቀ የባህል ሙዚየም ግንባታ የሚውል ይሆናል፡፡

የመደመር ትውልድ መጽሐፍን ስፖንሰር በማድረግ እና በመግዛት ሁሉም ዜጋ በትውልድ ግንባታ ሂደት የበኩሉን እንዲወጣም ርዕሰ-መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በ10 ሚሊየን ብር መጽሐፉን በመግዛት ለተማሪዎች እንደሚያበረክትም ቃል ገብተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶች፣ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡