Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ከተለያዩ የቻይና ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ለቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች ላይ  ገለጻ ተድርጎል፡፡

ባለሃብቶቹ በብረት፣ በሲሚንቶ፣ በጂኦተርማል፣ በማዳበሪያ ማቀነባበሪያ፣ በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ እና በሌሎቹም የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ በተለይ በሲሚንቶ፣ በግንባታ ግብዓት፣ በታዳሽ የሃይል ምንጭና በሌሎች ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Exit mobile version