የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሞሮስ ኘሬዚዳንት ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል

By Mekoya Hailemariam

March 30, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የኮሞሮስ ኘሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ምሽቱን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሰደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኘሬዚዳንት አዛሊ የመጡት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት የስራ ጉብኝት ለማድረግ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

#Ethiopia