የሀገር ውስጥ ዜና

ጅቡቲ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለሚላኩ ዕቃዎች ለወደብ ከምትከፍለው ላይ 82 ነጥብ 5 በመቶ ቅናሽ ማድረጓን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ

By Tibebu Kebede

April 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጅቡቲ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለሚላኩ ዕቃዎች ለወደብ ከምትከፍለው ላይ 82 ነጥብ 5 በመቶ ቅናሽ ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ድጋፍ የሚያስፈልጋትን ጎረቤት ሀገራቸው ኢትዮጵያን በማሰባቸው እጅግ አመሰግናቸዋለሁ” ብለዋል።