ስፓርት

ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ያስቆጠራቸው ጎሎች ከ100 አለፉ

By Meseret Awoke

March 29, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  ሌዮኔል አንድሬስ ሜሲ ለአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን ጎሎች ትናንት ምሽት ከ100 አሳልፏል፡፡

ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ካረቢያን ደሴትን ትላንት ምሽት በሳንቲያጎ ዴል ኤስትሮ 7 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡

የ7 ጊዜ ባሎን ዲ ኦር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በፈረንጆቹ 2006 አርጀንቲና በክሮኤሺያ 3 ለ 2 በተሸነፈችበት ጨዋታ የጎል አካውንቱን የከፈተ ሲሆን ፥ ትናንት ምሽት ለሃገሩ 102ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል፡፡

የጋብሬል ባቲስቱታን ሪከርድ በማሻሻል ለነጭ ሰማያዊዎቹ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆን የቻለው ሜሲ 7ኛ የብሄራዊ ቡድን ሀትሪኩንም መስራት ችሏል፡፡

ሜሲ ከፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲኖ ሮናልዶ እና ከኢራኑ አጥቂ አል ዳኢይ በመቀጠልም 3ኛው የዓለማችን ብዙ ጎል አስቆጣሪ ሆኗል፡፡