Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ሃርቢ ቡህ በኢትዮጵያ ከባንግላዲሽ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሃርቢ ቡህ በኢትዮጵያ ከባንግላዲሽ አምባሳደር ሙሐሙዱል ዓለም ካሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በድሬዳዋ በሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ መምከራቸውን የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል።
አምባሳደሩ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና፣ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን እንዲሁም የድሬዳዋ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የስራ እንቅስቃሴን መጎብኘታቸው ተጠቁሟል፡፡
ጉብኝቱ በድሬዳዋ የሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለማየትና ድሬዳዋ ከባንግላዲሽ ከተሞች ጋር የእህታማማችነት ከተማ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ጉእንደሆነ አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ም/ከንቲባና ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊው ሐርቢ ቡህ ለአምባሳደሩ በአስተዳደሩ የሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ውይይቱ በቀጣይ የሁለቱንም ከተሞች ትስስር በማጠናከር የባንግላዲሽ ባለሃብቶች ድሬዳዋ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ አንስተዋል።
Exit mobile version