አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማንን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቱን አስታውቋል።
ክለቡ ወጣቱን አሰልጣኝ ለውጥ ፍለጋ በሚል እንዳሰናበታቸው ደይሊ ሜይል አስነብቧል።
የቀድሞው የቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ፒ ኤስ ጂ እና ቼልሲ አሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ቱሼል የባቫሪያኑን ክለብ ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኔግልስማን ሙኒክን በፈረንጆቹ 2021 በአሰልጣኝነት ተረክበው ቡንደስሊጋ እና የጀርመን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን ከክለቡ ጋር አሸንፈዋል።
ሙኒክ በቡንደስሊጋው ከተቀናቃኙ ዶርትመንድ በነጥብ አንሶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲሆን በቻምፒየንስ ሊጉ ደግሞ በግማሽ ፍጻሜው ከእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ ጋር ይጫወታል።