Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያ ክልል የሕዝቡን ኑሮ በሚለውጡ አጀንዳዎች ላይ እየሠራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ በሚለውጡ አጀንዳዎች ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ገለጹ፡፡

የ2015/16 ዓ.ም የመኸር አዝመራ ዝግጅት እንዲሁም የክልሉ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ አወሉ አብዲ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አርሶ አደሩ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት እንዲኖረው የብድር አገልግሎት የሚያገኝበት ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዛሬ በተጀመረው የንቅናቄ መድረክ አማካኝነት 100 ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ዘንድሮ በክልሉ ቡሳ ጎኖፋ አማካኝነት ከ5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍም ተጠናክሮ ቀጥሏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ ሕገወጥ የእህል፣ የማዕድንና የእንስሳት ሀብት ንግድን እንዲሁም ኮንትሮባንድን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version