አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት በማድረግና በማልማት አብረን ተግተን ሠርተን እንበልጽግ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ምርጥ ሀገር እንዳለን ጠቅሰዋል።
በመልዕክታቸውም “ዓይናችንን ገልጠን ብንሠራ ለዓለም መስሕብ መሆን የሚችሉ በርካታ ቦታዎች በሀገራችን አሉ” ብለዋል።
አካባቢን መቃኘትና መፈተሽ እንደሚገባም በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።
“የኔ ያልነውን የጋራ ሀብት እናድርግ፤ እናልማ፤ አብረን ተግተን ሠርተን እንበልጽግ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!