Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ መጅሊስ እውቅና የሰጣቸው ወጣቶች ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ እያሰባሰቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ መጅሊስ እውቅና የሰጣቸው ወጣቶች 10 ሺህ ለሚደርሱ አቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ እያሰባሰቡ ነው።

ወጣቶቹ “እኔ እያለሁ ወገኔ አይራብም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ድጋፉን እያሰባሰቡ ያሉት።

ድጋፉ ለአንድ አባወራ 10 ኪሎ ዱቄት፣ 5 ኪሎ ሩዝ፣ 3 ኪሎ መኮረኒ፣ 2 ሊትር የምግብ ዘይት እና የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናን ያካተተ ነው።

ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አካላትም ፍል ውሃ አካባቢ ባለው ተውፊቅ መስጅድን ጨምሮ፥ በቄራ ሰላም መስጅድ እና ወይራ ሰፈር አልዮ መስጅድ ድጋፋቸውን ማድረስ እንደሚችሉም ወጣቶቹ ተናግረዋል።

እስካሁን ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አባዎራዎች የሚሆን ድጋፍ መሰብሰብ እንደተቻለም የድጋፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።

በተለያዮ ምክንያቶች ምግብ አብስለው መብላት ለማይችሉ ሰዎች በሶ፣ ቆሎ እና ብስኩት በ3 ኪሎ ግራም ታሽጎ 1 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ድጋፍ እየተደረገ ነው።

ድጋፉ ሁለት የተለያየ ቤተሰብን በማስተሳሰር በጎነትን በሚያጠናክር መልኩ እየተደረገ ይገኛል።

በአወል አበራ

Exit mobile version