ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገቡ

By Mikias Ayele

March 13, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ አስመራ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአስመራ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡