የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓመቱ ምርጥ የማይዋዥቅ የጭነት አገልግሎት ሰጪ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ ሆነ

By Alemayehu Geremew

March 13, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2023 “በአፍሪካ ቀጠና የዓመቱ ምርጥ የማይዋዥቅ የጭነት አገልግሎት የሚሠጡ አየር መንገዶች ሽልማት” ተርታ የፍጻሜ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተገለጸ፡፡

በተጨማሪም “የዓመቱ ምርጥ የማይዋዥቅ የጭነት አገልግሎት የሚሠጡ አየር መንገዶች ሽልማት” የመጨረሻ ዕጩ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

በዕጩነት የፍጻሜ ውድድር ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማቱን ለማግኘት የሚያስችለውን የመጨረሻ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት መጀመሩንም በመረጃው አመላክቷል፡፡