የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታሩ አል ፋይሰል ሆልዲንግስ ኩባንያ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

March 09, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታሩ አል ፋይሰል ሆልዲንግስ ኩባንያ ሊቀመንበር ሼክ ፋይሰል ቢን ቃሲም አል ታኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የኳታሩ አል ፋይሰል ሆልዲንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሊሰማራ በሚችልባቸው የንግድ አማራጮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

የአል ፋይሰል ሆልዲንግ  ኩባንያ የንግድ ልዑክ ቡድን በቅርቡ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እንዲደርግም ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የአል ፋይሰል ሆልዲንግ  ኩባንያ  በኳታር በዶሃ የሚገኝ ግዙፍ የግል የንግድ ኩባንያ ሲሆን በርካታ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡