Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጨምር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጨምር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ሙሳፋኪ ማሃማት ጥሪውን ያቀረቡት ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት “ዲጂታል ለሁሉም ÷ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት – የ 20 ዓመታት የማፑቶ ፕሮቶኮል” በሚል መሪ-ቃል ቀኑን አስቦት ውሏል፡፡

የዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት መሪ-ቃል በመረጃ እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚንቀሳቀስባቸው ጉዳዮች ጋር የሠመረ ነው ብለዋል ሊቀ መንበሩ።

ኅብረቱ በመረጃና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እና ሴቶች ዘላቂ ለውጥ እንዲያስመዘግቡ በዕቅዱ አካቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ዕድገት ምሉዕ እንዲሆን የሴቶችን ተሳትፎ በሣይንስ ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምኅንድስና ፣ ሥነ-ጥበብ እና ሒሳብ ዘርፎች ላይ ማሳደግ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

“ነገር ግን የሚቀረን መንገድ ረጅም ነው ፤ ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል” ብለዋል ባስተላለፉት መልዕክት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version