የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የሴቶች ቀንን በማስመልከት በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ አደረገ

By Shambel Mihret

March 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓለም የሴቶች ቀንን አክብሯል።

በዕለቱም አየር መንገዱ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ወደ ዛንዚባር የሚያደረገውን በረራ÷ ዋና አብራሪ፣ ረዳት አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጆችና ቴክኒሽያኖችን ጨምሮ በሙሉ በሴቶች እንዲመራ አድርጓል።

ከዚህ ባለፈም የአውሮፕላኑ  የአየር ትራፊክ፣ የበረራ ደኅንነትና የጭነት ቁጥጥር እንዲሁም የበረራ መለኪያ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚከናወን ስለመሆኑ ተመላክቷል።

የዓለም የሴቶች ቀንን በማስመልከት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሴቶች የተመሩ በረራዎችን ሲያደርግ ይህ ለ7ኛ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በረራው  የአየርመንገዱ የመጀመሪያ ሴት አብራሪ በሆኑት ካፒቴን አምሳል ጓሉ ነው የተመራው፡፡

በቅድስት ተስፋዬ