ቢዝነስ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል 

By Shambel Mihret

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም ከየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ የቤንዚን፣ የኬሮሲን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና ከባድ ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር በነበረው ዋጋ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ተገልጿል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ግን የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እንደተደረገበት እና በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር 70 ብር ከ60 ሣንቲም መሆኑን ሚኒስቴሩን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡