የሀገር ውስጥ ዜና

የኖርዌይ ሕዝብ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ሕጻናት የሚውል 10 ቶን አስቸኳይ ድጋፍ ሊያደርስ ነው

By Alemayehu Geremew

March 06, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኖርዌይ ሕዝብ ከተመድ ዓለም አቀፍ የሕፃናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ ሕጻናት የሚውል 10 ቶን አስቸኳይ ድጋፍ ሊያደርስ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኖርዌይ ዕርዳታ ጫኝ አውሮፕላን 10 ቶን አስቸኳይ ድጋፍ ይዞ ከዴንማርክ መነሳቱ ተጠቁሟል፡፡

አውሮፕላኑ የሕክምና ቁሳቁስ፣ የንፅሕና መጠበቂያዎችን እና ሌሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶችን ኮፐንሀገን ከሚገኘው ትልቁ የ“ዩኒሴፍ” ዓለም አቀፍ አፋጣኝ የዕርዳታ አቅርቦት እና ሎጅስቲክስ መጋዘን መጫኑን አቪየሽን 24 ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊየን የሚልቁ ሕፃናት የአስቸኳይ ሰብአዊ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በዮናታን ዮሴፍ