አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ በዛሬው እለት ሦስተኛው ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈው የ65 ዓመት ሴት የዱከም ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በተጓዳኝ በሽታ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ይከታተሉ የነበሩ መሆናቸውን ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል።
ግለሰቧ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በተጠቀሰው ዕለት ወደ ለይቶ ማከሚያ የገቡ ሲሆን ከዚህም ዕለት ጀምሮም በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል።
በመሆኑም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision