የሀገር ውስጥ ዜና

የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር ለአባቶቻችን ተጋድሎ ክብር በመስጠት ይሁን – አቶ ደስታ ሌዳሞ

By Tamrat Bishaw

March 01, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር ለአባቶቻችን ተጋድሎ ታላቅ ክብር እየሰጠን ሊሆን ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ 127ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመለክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡

ዓድዋ የጀግንነታችን ጥግ፣ የኢትዮጵያዊነታችን ክብር ከፍታ፣ የማንነታችን ጥንካሬ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራትና ድምቀት ነው ሲሉ አቶ ደስታ በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

የድል በዓሉ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና ክብር የማይደራደሩ ጀግና ህዝቦች መሆናቸውን ለዓለም ህዝብ ያስመሰከሩበት ነው ብለዋል።

በዓድዋ የአልደፈር ባይነታችን ወኔና ፅናታችን በተግባር የታየበት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የደመቀበት ገድል ነው ሲሉም ገልጸዋል አቶ ደስታ፡፡