የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከላትን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

April 10, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከላትን ጎበኙ።

በጉብኝታቸው ወቅት ከጤና ባለያዎች ጋር ተወያይተዋል።

ኢንጂነር ታከለ የጤና ባለሙያዎቹ ሙሉ ኑሯቸውን በማዕከላቱ በማድረግ እየሰጡ ላለው አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ በበኩላቸው የተለያዩ አገልግሎቶችና ግብአቶች ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አንስተዋል።

የተነሱት ችግሮች በትብብር እንደሚፈቱ የገለፁት ኢንጂር ታከለ የከተማ አስተዳደሩ የራሱን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለጤና ባለሙያዎቹ የጄኔሬተር፣ የምግብ ግብአቶችንና ጊዜ ማሳለፊያ ቁሳቁሶች ማበርከቱን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision