ቴክ

የአውሮፓ ኮሚሽን ሠራተኞች ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ ታገዱ

By Alemayehu Geremew

February 24, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአውሮፓ ኮሚሽን ሠራተኞቹን ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ አገደ፡፡

መተግበሪያውን ከሞባይላቸውም ሆነ ከኮሚሽኑ መገልገያ ኮምፒውተሮች ላይ እንዲያጠፉ መታዘዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኮሚሽኑ ውሳኔውን ያሳለፈው የድርጅቱን የሳይበር ደኅንነት ለማሳደግ እና ዲጂታል ሠነዶቹን ከጥቃት ለመታደግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ኮሚሽኑ ከ32 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት አስታውቋል፡፡

ቲክ ቶክ የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን የተጠቃሚዎቹን መረጃ ለቻይና መንግስት ያቀርባል የሚል ክስ ይቀርብበታል።

ቲክቶክ በበኩሉ ማኅበራዊ ሚዲያው ከሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች የተለየ እንደማይሰራ ገልጿል።

የኮሚሽኑ ሰራተኞች የቲክ ቶክ መተግበሪያ ያለበትን የግል ስልካቸውንም ቢሆን መጠቀም አይችሉም ነው የተባለው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሰራተኞቹ ቢበዛ እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 15 ድረስ ቲክ ቶክን ከስልኮቻቸው ማስወገድ ይኖርባቸዋል።