የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

By Amele Demsew

February 24, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት በፈተና ውስጥም ቢሆን የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ በርካታ ሰው ተኮር እንዲሁም የልማት ስራዎችን ሰርተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በግምገማው ህዝቡን ለማገልገል የተሄደባቸው መንገዶች ሁሉ እንደሚፈተሹና ታቅደው የተከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ውስንነቶች እንደሚለዩም አስታውቀዋል።

” ወደ ህዝቡ በመቅረብ መታረም ያለባቸው ሁሉ እንደሚታረሙ በተሰሩ አበረታች ስራዎች ሳንታበይ ሃይላችንን አጠናክረን ከምንጊዜውም በላይ ህዝባችንን ለማገልገል እንዘጋጃለን” ሲሉም ገልጸዋል።