የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 50 በመቶ የኪራይ ቅናሽ አደረገ

By Tibebu Kebede

April 10, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ50 በመቶ የኪራይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ረሻድ ከማል ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ወር ጀምሮ በሚያከራያቸው 18 ሺህ 153 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ላይ የኪራይ ቅናሽ ማድረጉን ተናግረዋል።

ቅናሹ የሚመለከታቸው ቤቶች በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች የሚገኙ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

ይህም ኮርፖሬሽኑ በየወሩ ከኪራይ ያገኝ የነበረውን ገቢ ከ120 ወደ 60 ሚሊየን ብር ዝቅ ያደርገዋልም ነው ያሉት።

አሁን የተደረገው ቅናሽ የመጀመሪያ መሆኑን ያነሱት ስራ አስኪያጁ በቀጣይ የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለው ጉዳት እየታየ ኪራይ እስከማስቀረት የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ ይችላልም ብለዋል።

በሃይለኢየሱስ ስዩም