Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሊሴ ነሜ በቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ሊዩ ዲያንክሰን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር በኢንቨስትመንት አጋርነት እና በኢንቨስትመንት ማስፋፋት ለማጠናከር መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ ቻይና መግባቱ ይታወሳል።

ልዑኩ በቆይታው ከቻይና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version