የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ከተመድ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

February 20, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ  የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም( ዩ ኤን ዲ ፒ)  በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን በመደገፍ ለሚያሳየው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የልማት ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ልማቶች ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ ሁልጊዜም ወጥነት ያለው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ ይህም በልዩ ልዩ የልማት መስኮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

አሁና ኢዚያኮንዋ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን ኤክስፖርት ማድረግ በመጀመሯ  መደሰታቸውን  ገልጸው÷ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የልማት ፕሮግራሙ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡