ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ድንገተኛ ጉብኝት እያደረጉ ነው

By Alemayehu Geremew

February 20, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካውፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ኪየቭ ድንገተኛ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

ጆ ባይደን በዩክሬን ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በፖላንድ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷“ጆሴፍ ባይደን፣ ወደ ኪየቭ እንኳን በደህና መጡ!”ም ብለዋል፡፡

የእርስዎ ጉብኝት እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ለሁሉም ዩክሬናውያን የድጋፍ ምልክት ነው” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡