የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጠ

By Shambel Mihret

February 20, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጠ።

እውቅናው የተሰጠው ለተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተማዎች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡