Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ ከተማ በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጠ።

እውቅናው የተሰጠው ለተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተማዎች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ የተመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ አንስተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው÷መርሐ ግብሩ ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎችን በማበረታታት ሌሎች ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን ለመፍጠር እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

ለውጤቱ መምጣት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ መምህራን፣  ወላጆችና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትንም አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version