የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 19, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል ጋር ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ኢትዮጵያ ከህብረቱ ምክር ቤት ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የተስማሙ ሲሆን÷ በተጨማሪም በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነትም የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል መደሰታቸውን ገልጸዋል።