የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አዲሱን የጅቡቲ ኤምባሲ መርቀው ከፈቱ

By Meseret Awoke

February 19, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በአዲስ አበባ የተገነባውን አዲሱን የጅቡቲ ኤምባሲ መርቀው ከፈቱ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢጋድ ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች መገኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።