Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ “ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚል እሳቤ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሠላም ሂደት በመደገፍ ላበረከረተችው አስተዋፅዖ አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከርም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን ነው አቶ ደመቀ የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ለሠላም ስምምነቱ ትግበራ ያሳየችው ቁርጠኝነት ደቡብ አፍሪካን ማስደሰቱን ና ሌዲ ፓንዶር መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ለቀጣይ የሠላም ስምምነቱ ተግባራዊነት እና ሂደት የሚጠበቅባትን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version