የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በቱርክ በደረሰው አደጋ የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷን አስታወቁ

By Mikias Ayele

February 17, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ኢትዮጵያ ባላት አቅም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱርክ ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን ለፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ገልጫለሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጇን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባላት አቅም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷን ገልፀዋል።