የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታካጊ ኬይ ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

February 17, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታካጊ ኬይ ጋር ተወያይተዋል።

በወይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና በጤና ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በቀጣይም በሁለትዮሽ የግንኙነት ማዕቀፍ ውስጥ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር እንደሚሠራ መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።