የሀገር ውስጥ ዜና

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By Alemayehu Geremew

February 15, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልኅ ሞሐመድ በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ለመሳተፍ ዛሬ አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡