አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ከ25 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ።
የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ ማህበረሰቡ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እንዲያገኝ ብሔራዊ የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና አምራቾች ላይ አስተዳራዊና ህጋዊ እምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተነግሯል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ህግን በተላለፉ 25 ሺህ 300 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህም1 ሺህ 684 የንግድ ተቋማት ላይ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን 153 የሚሆኑ የንግድ ባለቤቶች በእስራት እንዲቀጡ መደረጉን ተገልጿል፡፡
እንደ ካራንቡላ፣ ፑል፣መጠጥ፣ጭፈራ፣እና ሌሎች ብዙ ሰው የሚሰበሰብባቸው የንግድ ድርጅቶች በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ተዘግተው የሚቆዩ ይሆናል ብሏል ግብረኃይሉ።