Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኬንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኬንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኬንያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልፍሬድ ሙታ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ጉብኝት ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version