የሀገር ውስጥ ዜና

መድፈኞቹ በጉዲሰን ፓርክ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናገዱ

By Mikias Ayele

February 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሴናል በኤቨርተን የውድድር ዘመኑን ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

በጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤቨርተን በጄምስ ታርኮውስኪ የ60ኛ ደቂቃ ጎል አርሴናልን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድን ያሰናበተው ኤቨርተን በአዲሱ አሰልጣኙ ሾን ዳይክ መሪነት የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ኤቨርተን በ18 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

አርሰናል የዛሬውን ሽንፈት ተከትሎ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያሰፋበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።