የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ስምምነቱ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ

By Alemayehu Geremew

February 03, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሠላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴው ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የሰላም ድርድሩ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሃላላ ኬላ ነው፡፡