Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በለንደን ማራቶን ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 2023ቱ የለንደን ማራቶን የሴቶች ውድድር ትሳተፋለች፡፡

አትሌት  ያለምዘርፍ  ባለፈው ዓመት የተደረገውን የለንደን ማራቶንን ወድቃ በመነሳት በድንቅ ብቃት ማሸነፏ የሚታወስ ነው ።

የ21 ዓመቷ አትሌት 1 ሰአት ከ3 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ስትሆን በ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 29 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት የክብረወሰኑ ባለቤት ናት።

አትሌት ያለምዘርፍ ከኬንያዊቷ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ብሪጊድ ኮስጌ እና ከኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ፔሬስ ጄፕቺርቺርም ከባድ ፉክክር ይጠብቃታል ተብሏል፡፡

በውድድሩ ከያለምዘርፍ በተጨማሪ የሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮኗ አልማዝ አያና ከያለምዘርፍ በተጨማሪ እንድምትካፈል ከለንደን ማራቶን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version