አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኮቪድ-19 የሚያስከትለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ብድር የመክፈል ሂደትን ስለ ማዘግየትና የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የሚያስፈልገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በተመለከተ መምከራቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈም ከቀውሱ በኋላ የሚመጣውን የኢኮኖሚ ጉዳት መከላከል በሚያስችሉ እርምጃዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision